![]()
ESAT Ethiopia--Copyright protected
"ስለሀገር ፍቅር የሚያወሩ፣ ስለ ኢትዮጲያ ተራራ፣ ሸንተረር፣ ለምለም መሬት ምናምን-ምናምን የሚያወሩ ሰዎች አንዳንዴ ያሳዝኑኛል፣ ሌላ ጊዜ ያሳፍሩኛል"
ሟቹ የህወሓት መሪ መለስ ዜናዊ
ባለፈው እሁድ በተካሄደው 17ኛው ታላቁ ሩጫ ላይ ለመሳተፍ ባንዲራችውን በግንባራቸው አስረው፣ በእጃቸው እና በአንገታቸው አጥልቀው የሄዱ ወጣቶች ባንዲራቸው የኢህአዴግ ዓርማ የለበትም እየተባለ በነጭ ለበስ ደኅንነቶችና ፖሊሶች እየተዋከቡ እየተቀሙ ባንዲራው አስፋልት ላይ ተወርውሯል።
በቀዳማዊ ኃይለሥላሴም ሆነ በደርግ ዘመን የመንግስታቱ ዓርማ ቢኖርም ሕዝቡ ያንን እንዲያውለበልብ አይገደድም ነበር። ከ10 ዓመት በፊት የባንዲራ ሕግ ተብሎ ከወጣ ወዲህ ህወሓት ኢሀአዴግ የፈጠረው ዓርማ የሌለበት ባንዲራ ሕገ ወጥ ተብሎ ተፈርጇል። ሆኖም የቀድሞው ብቻ ሳይሆን ባልፉት 2 አስርተ ዓመታት የተወለደው አዲሱ ትውልድ ሳይቀር ሥርዓቱ ከሚፈልገው በተቃራኒ አያት ቅድመ አያቶቹ የተዋደቁለትን ባንዴራ መያዝ መርጧል። ምርጫው ሥርዓቱን አሰቆጥቷል፣ባንዲራ ነጥቆ እስከመጣል እርምጃ አስወስዷል።
ስለባንዲራውና የኢህአዴግ የግዳጅ ኮከብ ተወያይተናል::